ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት በሶስት ዙር ሲካሄድ የቆየው የተፋጠነ የማህበረሰብ ትግበራ /ሲ ኤም ፒ/ ፕሮግርም መድረክ ተጠናቀቀ፡፡

N2ከተለያዩ ጥሪ ከተደረገላቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የ2011 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና በ2012 የስራ እቅድ ትውውቅን መሰረት አድርጎ ሲካሄድ የነበረው ወርክሾፑ በተነሱ ሀሳቦች ላይ መግባባት በመድረስ በኮምቦልቻ ከተማ በቀን 25/04/2012 ተጠናቋል፡፡
ከፌደራል የኮዋሽ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች፣ ከሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ዋግ ህምራ፣ ኦሮሚያ፣ ሰሜን ሸዋ ዞኖችና 14 ወረዳዎች የተውጣጡ የዘርፉ አካላት የተሳተፉበ ትመድረክ ከታህሳስ 24-25/2012 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡


የትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያዎች መጸዳጃ ቤቶች እና የውሃ ጣቢያዎች ግንባታ አፈጻጸም ብቻም ሳይሆን አጠቃቀምና ጥራት ላይ በስፋት የተወሳበት የውይይት መድረኩ ፤ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የዘገየ ቢሆንም የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይም ውይይት በማድረግ የጋራ ግንዛቤ ተይዞበታል፡፡
‹‹ባለፈው ዓመት የዘርፉ አፈጻጸም ሌሎች ክልሎችም ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ ቢሆንም ፤ በአማራ ክልል ግን በሁሉም ወረዳዎች በጣም ከፍተኛና ምስጋና የተቸረው ስራ ተሰርቷል፡፡ በያዝነው ዓመትም ጥንካሬዎችን አስቀጥለን ከክፍተታችን ደግሞ በመማር ስኬታማ ተግባር እንደምናከናውን ባለሙሉ ተስፋነኝ፡፡›› ያሉት በፕሮጀክቱ የፌደራል ኮዋሽ የክትትልና ግምገማ ባለሙያ አቶ አበባው፤ የዚህን በጀት ዓመት ተግባር ደግሞ በቀሪ የስራ ወራት አንዱ ከሌላው በመማማር ስኬታማ ስራ መስራት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡
በውይይቱ የተለያዩ ሀሳብ፣አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፤የማጠቃለያ ሀሳብና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችም ከመድረክ መሪዎች ተላልፏል፡፡
የውይይት መድረኩ ባለፉት 2 ሳምንታት በባህር ዳር እና ደብረ ታቦር ከተሞች በተመሳሳይ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

መጪ ዝግጅቶች

No events

ጎብኚዎችን ቆጣሪ

032504
ዛሬ
ትናንት
በዚህ ሳምንት
ባለፈው ሳምንት
በዚህ ወር
ባለፈው ወር
ጠቅላላ
25
3
138
31557
1111
865
32504