ዋና ገፅ
ዶ/ር ማማሩ አያሌዉ ሞገስ
የአብክመ ዉሃ፣መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ የክልሉን የውሃ ሃብት ማስተዳደር፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማቅረብ፣ ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ያሉ የመስኖ አውታሮችን በመገንባት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ማስተላለፍና የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅና በማቅረብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ከክልሉ መንግስት የተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት በመሆኑ ይህን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ሰፊ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
በሁለተኛዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በገጠር ሁሉም አርሶ አደር ከሚኖርበት አካባቢ ከ1 ኪ/ሜ በላይ ሳይጓዝ 25 ሊትር ዉሃ በቀን ለእያንዳንዱ ሰው፤ በከተማ የህዝብ ቁጥራቸዉ ከ20,000 እስከ 999,999 ህዝብ ለሚኖርባቸዉ የክልላችን ከተሞች ከ50 እስከ 80 ሊትር ዉሃ በቀን ለሰዉ ለማዳረስና የህዝብ ቁጥራቸዉ ከ20,000 በታች ለሆኑ የክልላችን ከተሞች በ250 ሜትር ርቀት 40 ሊትር ዉሃ በቀን ለሰዉ ለማድረስ የተቀመጠዉን አዲስ ስታንዳርድ መሰረት በማድረግ የተጣለዉን ግብ ለማሳካት ሰፊ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት ከላይ በተቀመጠዉ ስታንዳርድ በዕትዕ-2 መጀመሪያ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ሽፋናችን በገጠር 53.46% በከተማ 54% እንደ ክልል 53.54% ላይ የደረሰ ሲሆን ከዚህ በመነሳት በአምስት ዓመት የተቀመጠዉን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ ስራ ተሰርቶ በከተማም ሆነ በገጠር የንጹህ መጠጥ ዉሃ ሽፋኑን ከፍ ማድረግ ተችሏል፡፡
Read more ...የደሴ ከተማ አስተዳደር የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወርቁ አሞኜ በ2011 ዓመተ ምህረት በሁሉም ተቋሞቻችን በድግግሞሽ 4ሺህ 573 ስዓት መብራት በመጥፋቱ ምክንያት 435ሺህ 600 ሜትር ኩብ ውሃ ሳይመረት ቀርቷል፤ በገንዘብ ሲተመንም በዝቅተኛው 2 ሚሊዮን 461ሺህ 140 ብር መስሪያ ቤቱ ገቢ ማጣቱንና በሥራ ላይ ያጋጠማቸው ችግሮችም የኔት ወርክ መቆራረጥ ችግር፣ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ችግር አለመፈታት፣በደርቅ ቆሻሻ ክፍያ አፈፃፀምና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያለው ችግር፤ ለገጠር ቀበሌ ኗሪዎች የንጹህ መጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል በጀት በክልሉና በከተማ አስተዳደሩ አለመሰጠቱ፤ በዉሃ ምርትና በደንበኞች አዳጊ ፍላጎት መካካል ሰፊ ልዩነት መኖሩ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑና አመራሩም በቀጣይ በጋራ ተቀናጅቶ ትኩረት በመስጠት እንዲሰራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ስብሰባዉን በንግግር የከፈቱት የአብክመ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ማማሩ አያሌዉ እንደገለጹት በአሁኑ ስአት በመጠጥ ውሃ አቅርቦቱ እና በመስኖ ግንባታው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረትና አዳዲስ አሰራሮችን በመቅረጽ መተግበር ካልቻልን ወደፊት የሚመጣውን የክልሉን ህዝብ የመጠጥ ውሃ ፍላጎት በአግባቡ ተደራሽ ማድረግ የሚያዳግተን መሆኑንና በመስኖ ልማቱ ዘርፍም ከዚህ ቀደም 100 ሽህ ሄክታር መሬት የሚያለሙ በርካታ ፕሮጀክቶችን መገንባት ብንችልም ከዲዛይን ጀምሮ እስከ ግንባታ ጥራት ድረስ ከፍተኛ ችግር እያጋጠማቸው ስለሆነ በእቅዳችን መሰረት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረግን እንዳልሆነ ተረድተን በቀጣይ እዚህ ውይይት ላይ እየተሳተፍን ያለን አካላት በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እናደርግ ዘንድ ከወትሮው በተለየ ተቀናጅተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ከተለያዩ ጥሪ ከተደረገላቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የ2011 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና በ2012 የስራ እቅድ ትውውቅን መሰረት አድርጎ ሲካሄድ የነበረው ወርክሾፑ በተነሱ ሀሳቦች ላይ መግባባት በመድረስ በኮምቦልቻ ከተማ በቀን 25/04/2012 ተጠናቋል፡፡
ከፌደራል የኮዋሽ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች፣ ከሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ዋግ ህምራ፣ ኦሮሚያ፣ ሰሜን ሸዋ ዞኖችና 14 ወረዳዎች የተውጣጡ የዘርፉ አካላት የተሳተፉበ ትመድረክ ከታህሳስ 24-25/2012 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ የመጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ባዘጋጀዉ በዚህ የዉይይት መድረክ በዉሃ አቅርቦትና ተደራሽነት፣ የዉሃ ብክነትና ብክለት እንዲሁም አዲስ በሚጀመረዉ የማስፋፊያ ፕሮጀክትን ትኩረት ተደርጎ ዉይይት ተደርጓል፡፡ ዉይይቱን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያሰጀመሩት የከተማዉ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር አህመድ የሱፍ እንዳሉት የከተማ አስተዳደሩ ለዉሃ አገልግሎት ጽ/ቤቱ በተገቢዉ መንገድ ዉሃ ለህብረተሰቡም ሆነ ለኢንዱስትሪዎች እንዲያደርስ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ እንደሆነና ዉሃ አገልግሎቱም ይህንን እገዛ በመጠቀም የተሻለ የዉሃ አቅርቦት እየሰጠ ይገኛል፡፡ አዲስ የሚጀመረዉን የማስፋፊያ ፕሮጀክትም በስኬት በማጠናቀቅ ይበልጥ ተደራሽነቱን የሚያሰፋ ይሆናል ብለዋል፡፡